ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
95

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት ሎት1. ነርሲንግ አስቴሽን  ስራ፣ ሎት 2. የህትመት ግዥ፣ ሎት 3. የኤሌክትሪኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት4. ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉል ሶፋ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁ /ቲን/ ሰርተፍኬት ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ዘወትር በስራ ሰአት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ 200/ሁለት መቶብር ብር/ ብቻ በመክፈል  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማነኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ  የድርጅቱ ክብ  ማህተም ፤ፊርማ እና አድራሻ  በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት እቃ  የሚሞሉት ጠቅላላ  ድምር ማነኛዉንም ግብር ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ  ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና  ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ባየር ላይ  ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት  በ8፡ 30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ሆኖ ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡:
  11. ተጫራቾች እቃዉን /አገልግሎቱን/ በራሳቸዉ ወጪ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል /በሎት/ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን  በተጠቀሰው  ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ 0588270427 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here