ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በስሩ ለሚያስተዳድራቸዉ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚዉሉ ባለ ሶስት እግር ባጃጆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ገንዘብ ያዥ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ 1 በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በማሸግ በአረጋዊያን ህንጻ ከሚገኘዉ ኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የካሌንደር ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ግ/ፋ/ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ዉስጥ በ21ኛዉ ቀን 3፡30 ሰዓት ይታሸግና በዛዉ ዕለት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ሆኖም 21ኛዉ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጥዋት 3፡30 ሰዓት ይታሸግና 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ፡፡
  10. የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት ባጃጆችን ባህርዳር ድረስ በማምጣት ማስፈተሸ/ለባለሙያ ማሳየት/ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ኢፓልኮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-47-67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here