በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር ኤሌክትሮኒክስ፣ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ እና ፍራሽ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከ200,000/ከሁለት መቶ ሺህ/ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ተኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት 10 በመቶ ውል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582270362 / 0582271188 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዊ ልማት ማህበር