በምሥ/ጎጃም ዞን በክላስተር ደረጃ ለአራቱ ወረዳዎች ማለትም የጎዛምን /ወ/ፍ/ቤት፣ የአዋባሰ ወ/ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት እና የአነደድ ወ/ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2016 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎቸ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 የህትመት ዉጤቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ::
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል:: ኮምፒዉተርና ተዛማች አቃዎች ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በታችም ጠቅላላ ዋጋ ቢሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳታፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው::
- ለሚገዙት እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20.00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ድረስ የጨረታ ሰነዱን የ4ቱንም ወረዳ ፍ/ቤቶች ከጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት አንድ በመቶ ከ1-4 ላሉ ሎቶች በባንክ በተረጋጋጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነድ መገዛት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማደረግ የጎዛምን ወ/ፍ/ቤት፣ በአዋበል ወ/ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት እና የአነደድ ወ/ፍ/ቤት የሁሎችም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ተኛው ቀን አስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች በተገኙበት ይታሸጋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት የ4ቱም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አ/ ቡድን ቢሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ጀምሮ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታ መክፈት የማይስተጓጎል መሆኑን እንገልፃለን::
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል::
- የጨረታ አሸናፊ በመሆን የሚቻለው በሎት በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑ ታውቆ የሁሉም እቃዎች ዋጋ መሞላትት ይኖርበታል:: እና በዋጋ በመሙያ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም ፊርማ እና ማህተም መደረግ ይኖርበታል::
- መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ሃያ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
- አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋ ውስጥ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅበታል::
- አሸናፊ ድርጅት አቃን በራሱ ትራንስፖርት የአዋባል ጠ/ፍ/ቤት፣ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት፣ የአነደድ ወ/ፍ/ቤቶችን ምስ/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚቀርብ ሲሆን የጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ደግሞ በራሱ ተቋም ንብረት ክፍል አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም::
- የመጫረቻ ሰነድ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምር ለሰላሳ ቀናት ፀንቶ ይቆያል::
- አሸናፊዉ ድርጅት በስማቸዉ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ::
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0587713129 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::