የጨረታ ቁጥር አብክመ ገቢ/የሚ/ተሸ/01/10/2017
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በክልል ቢሮዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በዞኖችና በወረዳዎች የሚገኙ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማለትም፡-(መኪናዎች ፣ ትራክተሮች ባጃጅ እና ሞተር ሳይክሎች ) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ/ ብር ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11፡00 ድረስ የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ተሽከርካሪ የሞሉትን የጠቅላላ ድምር ዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም 60 ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በአንድ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በአብክመ ገንዘብ ቢሮ ስም በማሰራት በአንድ ፖስታ ብቻ በማሸግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተሽከርካሪ ዋጋ የሞላበትን ገጽ ብቻ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በ02/11/2017 ዓ/ም 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 02/11/2017 ዓ/ም 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ተሽከርካሪዎችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11:00 ድረስ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በመሄድ በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ርክክብ የሚፈጸመዉም በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠዉ ቦታ ነዉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ በተናጠል በተሰጣቸው የሠሌዳ ቁጥር ወይም መለያ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በፖስታቸዉ ላይ ስም ከነአያት፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸዉ፡፡
- ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-220-45-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ባህር ዳር ከተማ ከድሮዉ ዲፖ አካባቢ ይገኛል፡፡
የአብክመ ገንዘብ ቢሮ