ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
19

በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተሁለደሬ ወረዳ ለሚገኙ ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች ፣ሎት 3. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ሎት 4. በUNDP በጀት የህክምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለዉ መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሳሪያ 10000 (አስር ሽህ ብር) ፣ ለጽዳት ዕቃዎች 6000.00 (ስድስት ሽህ ብር)፣ ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች 00 (አስር ሽህ ብር)፣ ለህክምና መሳሪያዎች 10000.00 (አስር ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከዻጉሜ 3/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታዉ መስከረም 13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበአል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ወይም በድምር ዋጋ ነዉ፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ እስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
  11. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት እቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  13. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡
  14. ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታዉ ዉጭ ሆነው ወደ ፊትም በመንግስት ጨረታው እንዳይሳተፍ ይደረጋሉ፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here