በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የመገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኔዬን ኃ.የተ. የተለያዩ የግንባታ እቃወችን 1ኛ. ሎት 1. የቆቦ አሸዋ ብዛት 208 ሜ.ኩብ ፣ 2ኛ. ሎት 2. የላሊበላ አሸዋ ብዛት 208 ሜ.ኩብ ፤3ኛ. ሎት 3. የተለያየ መጠን ያላቸው ጣውላዎች ብዛት 172 ፣4ኛ. ስሚንቶ ፒፒሲ ብዛት 440 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራች መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሶስት በመቶ ፣ በመገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- የግዥው መጠን ከ500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙት ዕቃዎችን አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከመገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን የግንባታ ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት /በምድብ/ ዋጋ ይሆናል፤ ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ ።
- የጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 የጨረታ ሰነዱ ተሽጦ በ10 ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያአሸነፉትን የግንባታ ዕቃዎች ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን በደ/ታቦር ከተማ ከሚገኘው የግንባታ ቦታ ላይ ማቅረብ አለበት ፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በማስታወቂያው ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 14 19 927 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
መገናኛ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተ.