ግልፅ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

ሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢትርፕራይዝ ሎት1. መድሀኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎችን ፣ሎት2. የፅፈትና የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት.3 የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 4. የመኪና ጎማ እና እስፔር ፓርቶችን፣ ሎት5. ለተማሪዎች የምግብ አግልግሎት የሚውሉ ነጭ ጤፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፤
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ስራ ክፍል የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መዉሰድና ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግና በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢትርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. የሚገዛዉ ዕቃ ከ200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ በእያንዳንዱ ሎት. 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፏቸዉን ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታው ሰነድ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤ ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡ ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጨራቾች ከመክፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የምንከፍት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 ቀን በኃላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር 3በመቶ እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙላት የኖርባቸዋል፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 59 13 56 ወይም 09 13 42 26 44 ይደዉሉ፡፡
  13. አድራሻ በአዊ አስ/ ዞን እ/ከተማ በእንጅባራ ዩንቨርስቲ ሱታና የንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here