በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ 3 አይነት ግዥዎችን ሎት1. የፅዳት አውት ሶርስ፣ ሎት2. የምግብ አቅርቦት አውት ሶርስ ፣ሎት3. የጥበቃ አውት ሶርስ በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- የግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የፅዳት አውት ሶርስ እና የጥበቃ አውት ሶርስ ከሁለት የመንግት መ/ቤት ወይም ህጋዊ የግል ድርጅት ተቋማት የአንድ አንድ አመት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 300 ብር በመክፈል
ከግ/ፋ/ንብ/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በሎት የወጡትን 3ቱንም አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩ ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አስር በመቶ የውል ማስያዣ ያስይዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ አለም ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ አለም ሆስፒታል
ባህርዳር