ግልፅ የጨታ ማስታወቂያ

0
203

በሰሜን ወሎ ዞን የጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተሮች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. ብትን ጨርቅ ደንብ ልብስ፣ ሎት 5. የተዘጋጁ ልብሶች ደንብ ልብስ፣ ሎት 6. የሃገር ውስጥ ፈርኒቸር ከኤምዲኤፍ የተሠሩ ሎት 7. የሃገር ውስጥ ፈርኒቸር ከብረት የተሠሩ፣ ሎት 8. የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 9. መንገድ ሥራ ተቋራጮች በየዘርፉ ከተሰማሩ ነጋደዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ነጋዴዎች /ድርጅቶች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

ሕጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት በፊት መሆኑን መገለጽ አለበት፡፡

የሚገዙ የዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

የመንገዱን ሥራ ዝርዝር ከጨረታ መመሪያውና ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

የተዘጋጀውን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይቻለም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ናሙና ማየት ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማየት ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ለቀረበበት ዕቃ በቀረበው ናሙና መሰረት የሚያቀርቡ መሆን አለበት፡፡

የሚያቀርቧቸውን አቅርቦቶች /ማቴሪያሎች/ የጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ተጫራቾች የራሳቸውን ስፔስፊኬሽን ጨረታ ሰነድ ላይ ማስቀመጥ አለባቸውም፡፡

ከሎት 1. አስከ ሎት 8. ያሉት ግዥዎች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉና የገዙትንም የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ በማሸግ በዚሁ የሥራ ሰዓት በጋ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ይህ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ሎት 9. መንገድ ሥራ ተቋራጩ/ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉና የገዙትንም የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ በማሸግ በዚሁ የሥራ ሰዓት በጋ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ይህጨረታ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

በጨረታው አካሄድ ቅር የተሰኘ ተጫራች ካለ ጨረታው ከተከፈተ አስከ 5 ተከታታይ ቀናት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አስከ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ ቀርቦ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በየሎት አይነቱ በሎት ድምር ውጤት ነው፡፡

ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድረጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት 1. ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር/፣ ሎት 2. 40,000.00 /አርባ ሽህ ብር/፣ ሎት 3. 2,000.00 /ሁለት ሽህ ብር/፣ ሎት 4. 1,500.00 /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር/፣ ሎት 5. 2,000.00 /ሁለት ሽህ ብር/፣ ሎት 6. 5,000.00 /አምስት ሽህ ብር/፣ ሎት 7. 800.00 / ስምንት መቶ ብር/፣ ሎት 8. 4,000.00 /አራት ሽህ ብር/ እና ሎት 9. 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ ብር/  በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ያህል ዋስትናው ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡

አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ፣ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ የውል ማስያዥያው የቆይታ ጊዜው ውሉ ከተወሰደ በኋላ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ያህል ዋስትናው ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡

የዕቃው ርክክብ የሚፈጸመው ጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሲሆን የዕቃውን ማጓጓዥያ ወጭ በአሸናፊው /በዕቃ አቅራቢው/ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ አሸናፊው የሞላው ዋጋ ሳይቀየር መሥሪያ ቤቱ አቅርቦቱን ሃያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ  መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 19 00 47 ወይም 09 95 46 22 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here