የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ለግብአት አቅርቦትና ስርጭት ገጠር ፋ/የሥራ ቡድን ለመስኖ አት/ፍራ/ውሃ አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚውሉ የአቡካዶ እና ማንጎ ዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው::
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግብርና መምሪያው የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት ገጠ/ፋይ የሥራ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ለዚህ ጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ(spasfication)፣በዘርፋ እና ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ነው::
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ መሥሪያ ቤቱ ወይም ጽ/ቤት በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና መምሪያው የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት የሥራ ቡድን ቢሮ በ16 ኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል:: በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር 058 775 08 81 በመላክ በስልክ ቁጥር 058 775 08 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::