የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የቢሮው፣የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዮት እና የምዕራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤት የ2016 ዓ/ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ አመታዊ የቢሮዎች፣የሽንት ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት/ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች/ ግዥ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊ ድርጀቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር ( ቲን ) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር ከ200.000.00 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ( ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቀረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ አመታዊ የቢሮዎች፣የሽንት ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት /ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን/ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 /28/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም /የአገልግሎቱን/ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የስባሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፤ቅዳሜ፣እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በጨረታው ውስጥ ካለ ሲሞሉ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205000 /0582266180 /በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ለበለጠ መረጃ 0582266180 & 0583205000 * 725 Fax 203457 & 220673 ማግኘት ይችላሉ፡፡