ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
154

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- Lott 1. Impedance starting control panel /switch board, Power Cables, Dewatering submersible and surface pump፣ Lott 2. Generator and all accessories, Lott 3. Mechanical Spare parts for surface motor፣ Lott 4. ለብየዳ የሚስፈልጉ እቃዎች፣ Lott 5. butt fusion welding machine፣ Lott 6.  different size Pipe fittings and Accessories, HDPE pipe Compression fittings፣ Lott 7.  Galvanized Steel Pipes, Hand Tools/ Equipment፣ Lott 8. Water Meters and Woltman Continuous Type Recording Water Meters፣ Lott 9. የውሃ ጥራት ሪኤጀንት እና መሳሪያዎች እና Lott 10. የጽዳት መገልገያ እቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉን፣ ኮፒውን እና ሲፒኦ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /un Conditional  Bank Garanty/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ  በመቅረብ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ  በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባሕር ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 320 50 79  ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here