የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል::ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ::
- በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የታደሠ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ:: የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ /ቲን/ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
- ለማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በመምጣት ሠነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ3ዐ/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው::
- በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ሕጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም::
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::
- በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 03 41/058 218 11 94 መጠየቅ ይቻላል::
- ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት