የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የቢሮ፣ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዮት፣ የምዕራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤት፣የከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት እና የUIIDP የ2016 ዓ/ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ አላቂ፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የተለያዩ የፅህፈት መሣሪያዎችና ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. ፈርኒቸሮች፣ ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ሎት 5. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ከነካላማዳሪያው እና ሎት 6. የመኪና ዲኮር/የመኪና ታፒሰሪዎች/ ግዥ በመደበኛ በጀት ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፋሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ( ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ከፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27 /28/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፤ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሎት 4. የተጠቀሱትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሲሞሉ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205000 /0582266180 /በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ