ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
164

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመደበኛ፣ በተራድኦ እና በውስጥ ገቢ በጀቶች ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ ዲኮር፣ የብስክሌት ጎማ፣ የህክምና ግብዓቶች፣ የህክምና መሳሪያ ጥገና፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ እድሳትና ጥገና ሥራ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦት በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ 2ኛ ዙር ዓመታዊ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈረቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ለቢሮ እድሳትና ጥገና ሥራ ደረጃ 8 እና በላይ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን / እና ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የህክምና ግብዓት እና የህ/መሣሪያ ጥገና በነፃ ማግኘት ሲችሉ ሌሎችን ግን ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ 00 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከነ ቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ኢንስቲትዩቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ16 ኛው ቀን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋት 3፡30 ታሽጎ በዚሁ 3፡35  ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን ለእያንዳንዱ የሎት ምድብ 5,000.00 /አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /ስፒኦ/፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ኢንስቲትዩቱ የጨረታ አሸናፊው ከተለየ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት 20 በመቶ በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል ይዞ የማስቀረብ መብት ይኖረዋል፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊዎች የሚለዩት በነጠላ  ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  15. ኢንስቲትዩቱ የሚሰበስበው ሁለት በመቶ በዊዝ ሆልድ ብቻ ነው፡፡ አድራሻ ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ጎን ነው፡፡

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here