በደቡብ ጐንደር ዞን የክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ለመሥራት ስሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ክሊራስ መረጃ ያላቸው፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መረጃ፣ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- ከተ.ቁ 1 እስከ 3 ያሉት ፖስታው ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡ ሰነዱን ክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6/8 ያገኛሉ፡፡ የድርጅቱን ስም ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ያገኛሉ፡፡ የአንዱ ሰነድ ዋጋ 400.00/አራት መቶ ብር/ ነው፡፡ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብታችን እንደተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከጥዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 12 ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ15ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ 058 251 01 37 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ቢሮ ቁጥር 12 ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ አንድ በመቶ ሕጋዊ በሆነ ባንክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በተቋሙ ገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡