ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
124

የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት፤ሎት1. የእንስሳት መድሀኒት በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የቫት ተመዝጋሚ የሆኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሎት በተጠቀሰው እስፔሲፍኬሽን መሰረት ማቅረብ እና ያሸነፉትን በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና የማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በጉባላፍቶ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ስም እና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በሎቱ የተገለጸውን እቃ ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡
  7. ተ/ቁ1. ሎት.1 ሰነድ በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ /ብር  በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡የመንግስትን ጥቅም የማይጎዳ ሁኖ ከተገኘ ዉለታ 20በመቶ ድረስ ከፍ እና ዝቅ ብሎ ዉለታ መዉሰድ የሚቻል ሲሆን  እንዲሁም በስድስት ወር ዉስጥ እንደ አስፈላጊነቱ ከተወሰደዉ ዉለታ ላይ ቀጥታ ግዥ መ/ቤቱ እስከ 30በመቶ ሊፈጽም ይችላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናዉንና ፎቶ ኮፒዉን ከነማስረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ የድርጅት ስምና አድራሻ በመግለጽ በድርጅተዎ ማህተም ተረጋግጦ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ዉሎ በአስራ ስድስተኛው ቀን 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 በግዥ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን ለሁሉም ጨረታ የጨረታዉ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ ለሁሉም ጨረታዎች  ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ተሸጋግሮ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ 5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የእንስሳት መድሀኒት ብር 15‚000/አስራ አምስት ሽህ/ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠው የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ / ፣በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ጨረታውን ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዋና ገንዘብ ያዥ መሂ በማስቆረጥ ኮፒ አድርገዉ ኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ፤ እንዲሁም የሚያሰሩት የባንክ ዋስትና ለጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ 60 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዉለታ ማስከበሪያ ቢያንስ 90 ተከታታይ የስራ ቀናት ዋስትናዉ ቆይታ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
  11. የጨረታዉ አሸናፊ ከታወቀ በኃላ አሸናፊው ውል ከወሰደ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከ 20 ቀን በኋላ ይለቀቃል ፣ የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ 10በመቶ በባንክ በተረጋገጠው የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ባልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና/ኦርጅናሉን/ የዋጋዉን ጠቅላላ ዋጋ በማስያዝ በጉ/ወ/ፍትህ/ጽ/ቤት በኩል ውል ይወስዳል፡፡
  12. ተጫራቾች የምትሞሉት የጨረታ ዋጋ ለስልሳ ተከታታይ የስራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም በሙሉ እንዳስረክቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፃማል፡፡ በተጨማሪ በጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አሸናፊ ከሆነ በኋላ እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም ፡፡
  14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና መጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያድርጋል በህግም ያስቀጣል ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
    1. ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ በቁጥር 0334310736 ወይም 033331-0157 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
    2. ስለትክክለኛነቱ የጥራት ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ስም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
    3. ውድድሩ በሎት በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች ሁሉንም የእቃ አይነቶች የመጫረቻ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ አንድም ይሁን ከአንድ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here