ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
159

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለ2017 ዓ.ም በካፒታል በጀት በማ/ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ የኖራ ማቃጠያ፣ መሃዝን፣ ላብራቶሪ፣ የጥበቃ ቤት፣ መፀዳጃ ቤት እና አጥር የያዘ ፋብራካ/ኘሮጀክት ግንባታ ሁሉንም ችሎ የሚሠራ ኮንትራክተር ደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ የሆነ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጠቅላላ ዋጋ /በሎት/ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የብቃት ማረጋገጫ በዘርፋ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ለእያንዳንዱ ሰነድ በፖስታ ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በነፃ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የግንባታ ሥራው ከተጀመረበት ቢበዛ በ220 የሥራ መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
  8. በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርኘራይ ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ እድልን ለማስፋትና ለማበረታታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ.ም ላይ የተመሰረተ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለ90 ቀናት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የቴክኒካል መመዘኛ መስፈርቱን የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ21ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሙሉ በሙሉ ማንበብና ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 202 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 97 04 በሥራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. የአብክመ ሴ/ህ/ጉ/ቢሮ ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊትለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 እንገኛለን፡፡

የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here