ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
122

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የመሥሪያ ቤቱ ንበረት ለሆኑት የተለያዩ ከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማ ከነ ካላማዳሪውና ከነፍላፑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. በስሙ የታተመ ማሕተምና ደረሰኝ ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 50,000,00 /ሃምሳ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ11/02/2017 ዓ/ም እስከ 5/02/2017 ዓ/ም 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በቀጣዩ ቀን በ6/02/2017 ዓ/ም ቀን በ4፡00 ይከፈታል ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት እንገደዳለን፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች በባሕር ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባሕር ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here