ግራንድ ካንዬን ብሔራዊ ፓርክ

0
113

የታላቁ ሸለቆው መገኛ በአሜሪካ ሰሜን ምእራብ አሪዞና ግዛት ነው፡፡ ሸለቆውን በ1540ዎቹ እ.አ.አ ስፔናውያን አሳሾች ነበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኙት፡፡

በኮሎራዶ ወንዝ ለዘመናት የተሸረሸረው ሸለቆ ለመስህብነቱ ዋነኛው ገፅታ ነው፡፡

ግራንድ ካንዬን የካቲት 16 ቀን 1919 እ.አ.አ በብሔራዊ ፓርክነት የተመሰረተ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 1,217, 262 ሄክታር ወይም 4926 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል፡፡

የብሔራዊ ፓርኩን ድንበሮች የመለየት፣ የጥበቃ እና የማቋቋሚያ ደንቦች ዝግጅት እና ማስፋፊያዎችን የማፀደቅ ተግባራት በ1919 እ.አ.አ በ1932፣ 1969፣1975፣ ተከናውነዋል፡፡

ታላቁ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ በ1979 እ.አ.አ ጥቅምት 26 ቀን የዓለም ቅርስ ሆኖ ለመመዝገብም በቅቷል፡፡

በሸለቆው ጐብኚዎች የሚበዙባቸው ደቡባዊ እና ሰሜናዊ ክፈፍ ወይም ጠርዝ እና አጐራባች ቀጣናዎች ናቸው፡፡ ቀሪው የፓርኩ ክፍል ወጣገባ የሚበዛበት በእግርም ሆነ በጋማ ከብት ለመጓጓዝ አስቸጋሪ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በፓርኩ ከሚገኙት ደቡባዊ እና ሰሜናዊ ቀጣናዎችም ደቡባዊው ቀጣና 90 በመቶ ለሚሆኑ ጐብኚዎች ቀዳሚ፣ ተመራጭ መዳረሻ ነው፡፡ የታላቁ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ዋና መስሪያ ቤት በደቡባዊው የሸለቆው ቀጣና መግቢያ ላይ ነው የሚገኘው፡፡

የፓርኩ ዋና መስሪያ ቤትም የሚገኘው በሸለቆው ደቡባዊ ጠርዝ መግቢያ ላይ በተመሠረተው የታላቁ ሸለቆ ሰፈር ነው፡፡

የፓርኩ ደቡባዊ ቀጣና ከአገራቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሱ መንገዶች መዳረሻ ነው፡፡ በደቡባዊ ቀጣና መግቢያ ላይ ካለው መንደር ማረፊያ፣ የነዳጅ፣ ምግብ እና መጠጥ፣ የመታሰቢያ ቁሶች መሸጫ፣ ሆስፒታል እና ቤተእምነቶች የመሳሰሉ አገልግሎት መስጫዎች ይገኝበታል፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ናሽናል ፓርክ፣ ዘ ካንዬን፣ የሎው ስኩተር፣ዊክፒዲያ  ድረገፆችን ተጠቅመናል፡፡  ::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የታኅሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here