ግብርናውን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቷል

0
144

በምርት ዘመኑ ዘመናዊ የግብርና አሠራርን በመከተል የተሻለ ምርት ለማግኘት በትኩረት እየሠራ መሆኑን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ስማቸው ለበኩር እንደተናገሩት ዞኑ ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ ነው።

እንደ ምክትል ኃላፊው ማብራሪያ በ2017/18 የምርት ዘመን በብሔረሰብ አስተዳደሩ 406 ሺህ 246 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል። እስካሁንም 404  ሺህ 466 ሄክታር መሬቱ ታርሷል። ከዚህ ውስጥ 24 ሺህ 795 ሄክታር መሬት  በትራክተር መታረሱን የተናገሩት  አቶ አዲሱ በአጠቃላይ እስካሁን 304 ሺህ 771 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል ብለዋል።

በዞኑ የእርሻ ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት እየተሠራ መሆኑን ያነሱት አቶ አዲሱ ለአብነትም 81 የእርሻ ትራክተር ጥቅም ላይ መዋላቸውን ጠቅሰዋል።

እንደ ምክትል ኃላፊው ማብራሪያ በምርት ዘመኑ 856 ሺህ 660 ኩንታል ሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዷል። እስካሁንም 418 ሺህ 612 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተሠራጭቷል። በተጨማሪም የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና ሌሎችን ጨምሮ ከ11 ሺህ 856 ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ተደርጓል። የአፈር አሲዳማነትን በኖራ ለማከም ሰባት ሺህ 21 ኩንታል ኖራ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልፀዋል።

የአፈር አሲዳማነት በአማራ ክልል በብዙ አካባቢዎች በመስፋፋቱ ከፍተኛ ስጋት መሆኑ ይታወቃል፤ ይህም በከፍተኛ ዝናብ እና በመሰል ምክንያቶች አፈር የሚይዛቸው ለሰብል ዕድገት መሠረት የሆኑ ንጥረ ነገሮች ሲመናመኑ  (በጎርፍ ሲወሰዱ) የሚከሰት ነው፡፡

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በ2017/2018 የምርት ዘመን 17 ሚሊዮን 792 ሺህ 264 ኩንታል ምርት ለማግኘት በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።

(መልካሙ ከፋለ)

በኲር የሐምሌ 28  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here