በስዊድን ሄልሲንቦርግ የምትኖር የ24 ዓመቷ እናት በልጇ ግንባር ላይ እንቁላል ስትሰብር ታዳጊዋ የምታሳየውን ምላሽ በቪዲዮ ቀርፃ ቲክቶክ ላይ በመልቀቋ ተከሳ የተፈረደባት መሆኑን ባለፈው ሳምንት ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
በ2023 እ.አ..አ በትንንሽ ልጆቻቸው ግንባር ላይ እንቁላል በመስበር ሲቀልዱ ቀርፀው በማህበራዊ ድረ ገጽ ያጋሩ ነበር::አብዛኛዎቹ በሳቅ የታጀቡ እና አስደሳች ተደርገው ይታዩም ነበር፡፡
የስዊዲናዊቷ ወጣት እናት በሴት ልጂ ግንባር ላይ እንቁላል ስትሰብር የተቀረፀውን ቪዲዮ ተመልካች (views) ለማግኘት መፈፀሟ ከተመልካች በቀረበ ጥቆማ ልትከሰስ ችላለች::
ሁነቱ የተፈፀመው ባለፈው የበጋ ወቅት ነበር::የ24 ዓመቷ እናት የቀረፀችውን ቪዲዮ በቲክቶክ ስትለቅ መቶ ሺህ እይታን አስገኝቶላታል::ነገር ግን ከተመለከቱት አንዱ ለፓሊስ በማመልከቱ እናት በልጇ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ተጠርጥራ ትከሰሳለች፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ እናት ልጇን ኬክ እንደሚሰሩ ነግራት በማብሰያ ቤት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣት እንቁላል ግንባሯ ላይ ልትሰብር ስትል እምቢታዋን ስትገልጽ ወይም ደስተኛ አለመሆኗን ምስሉ አመላክቷል፡፡
ጉዳዩን የያዙት አቃቢ ህግ ሲሲሊያ አንደርስን የተቀረፀውን ቪዲዮ ተመልክተው እናት ልጇን ስታጠቃ በቲክ ቶክ በርካታ ተመልካች ለማግኘት መልቀቋ የማይታመን ድርጊት መሆኑን ነው ለጋዜጠኞች የተናገሩት፡፡
አቃቢ ህጓ አጣርተው ባቀረቡት ክስም ታዳጊዋ ከእናቷ ጋር ኬክ እንደምትጋግር አስባ ደስተኛ እንደነበረች እና ድንገት በእናቷ በተፈፀመባት ድርጊት ተመልካች ሳቢ ምላሽ ለመቅረፅ ግንባሯ ላይ እንቁላል መስበሯን አስርድተዋል:: ይህም ግዴለሽነት የጐደለው ድርጊት መሆኑን ነው ያሰመሩበት፡፡
በመጨረሻም እና በገንዘብ እንዳትቀጣ የተፈረደባት መሆኑን ነው በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው (ታምራት ሲሳይ)
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም