ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጉዳት እያስከተሉ ነው

0
188

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንደ ሀገር የሚያደርሱት ማኅበራዊ፣ ሥነ ልቦናዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑን የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ተናግረዋል።

የክልሉ ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ እንዳሉት ደግሞ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሁሉም እገዛ ያስፈልጋል። በተለይ በቅርቡ ክልሉ የገጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲባባሱ ምክንያት እየሆነ ነው።

ቀደም ብሎም ተጠያቂነት ላይ የሚስተዋል ውስንነት እንዳለ በማንሳት የጸጥታ ችግሩ ደግሞ ሌላ መሸሸጊያ እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ትምህርት የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስወገጃ ዋነኛ መሣሪያ ቢሆንም አሁን ላይ በክልሉ ከአራት ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል ብለዋል።

ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ በመሆናቸው ለሕገ ወጥ ስደት፣ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለጾታዊ ጥቃት ጭምር እያጋለጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት በጥቃት ፈጻሚዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ከተሳታፊዎች ተነስቷል።

በሀገራችን የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ከሚያከትሉት ማኅበራዊ ቀውስ ባሻገር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን አራት በመቶ ይቀንሳሉ ተብሏል።

(ማራኪ ሰውነት)

በኲር የታኅሳስ 21  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here