ጣናነሽ 2 ወደ መዳረሻዋ ባሕርዳር ከተማ ደርሳለች። ከጅቡቲ ዶላሬ ወደብ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም መነሻዋን ያደረገችው ጣናነሽ 2 ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ነው ባሕር ዳር ከተማ የገባችው። ጀልባዋ የጣና ሐይቅን የውኃ ትራንስፖርት ለማዘመን እና የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም ስበት ማዕከልነት ለማሳደግ ትልቅ አቅም እንደምትሆን ተገልጿል።
150 ሜትሪክ ቶን ክብደት እና 38 ሜትር ርዝመት ያላት ጣናነሽ 188 ሰዎችን የመያዝ አቅም አላት፡፡ ለጎብኚዎች እና ለነዋሪዎች ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደምትሰጥ የምትጠበቀው ጀልባዋ በደረሰችባቸው አካባቢዎች ሁሉ ሕዝቡ ደማቅ አቀባበል እያደረገ ሸኝቷታል፡፡
ጀልባዋ ባሕር ዳር ከተማ ለመድረስ ሦስት ወር ከ25 ቀናትን ሲወስድባት የጉዞ አባላቱ ከፍተኛ ውጣ ውረድን አሳልፈዋል፡፡ የጉዞ አስተባባሪው ሳምሶን ገብረስላሴ የጉዞ ሂደቱ ሲበዛ ፈታኝ እንደነበር አስታውሷል፡፡ ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገዶች በጽናት ታልፈው ጀልባዋን አገልግሎት ከምትሰጥበት ቦታ ማድረስ ልዩ ትርጉም እንዳለው ተናግሯል፡፡ ሁሉንም ፈታኝ ክስተቶች ያለፍናቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር ነው ብሏል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ጋሻው እንዳለው ጀልባዋ በአንድ ጊዜ የምትይዘው የሰው ብዛት፣ ፈጣንነቷ፣ የተገጠመላት ቴክኖሎጂ እና ምቾቷ ጎብኚዎችን ከመሳብ ባሻገር የቆይታ ጊዜን በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንደሚኖራት ጠቁመዋል፡፡
በጣና ሐይቅ ውስጥ እና በዙሪያው ያሉ የመስህብ ሀብቶችን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዘመናት ይህንን ፍላጎት ለመመለስ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጥ የነበረው በታሪካዊቷ ጣና ነሽ ቁጥር አንድ ጀልባ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
አሁን ያለውን የቱሪዝም ፍላጎት እና አቅም ነባሯ ጀልባ ብቻዋን የምትቋቋመው እና የምትሸከመው እንዳልሆነ መምሪያ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ አሁን የመጣችው ጣናነሽ 2 ይህንን ችግር ለመሻገር አቅም እንደምትሆን ገልጸዋል።
በመዳረሻ አካባቢ ያለው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲበራከት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራው እንዲጨምር፣ በመዳረሻ ቦታዎች ሁሉ የሚኖረው
(ስማቸው አጥናፍ)
በኲር የሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም