ጥፋተኞች ተቀጡ

0
315

የስነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ  አመራርና ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ::

በ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከቀረቡ 95 ጥቆማዎች 36 አመራርና ሠራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦ እርምጃ ተወስዷል፤ ቀሪዎቹ በዲሲፕሊን ኮሚቴ በመታየት ሂደት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በ2015 በጀት ዓመት ጥቆማ ቀርቦባቸው እርምጃ ሳይወሰድባቸው በሂደት ላይ በሚገኙ ጉዳዮች ላይ ክትትል ተደርጎ በ16 አመራርና ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ነው ያለው።

በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው የስራ ሂደቶች መካከል የአዲስ ኃይል ጥያቄ 57 በመቶ እና የአስቸኳይ ጥገና 13 በመቶ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ካለፈው በጀት ዓመት ተላልፈው በሂደት ላይ የነበሩ ጥቆማዎችን ጨምሮ በ51 የተለያዩ የስነ-ምግባር ጥሰቶች 108 አመራርና ሰራተኞች ጥቆማ ቀርቦባቸዋል፡፡      ከነዚህም ውስጥ 17 የፅሁፍ፣ 31 የደመወዝ፣ 2 ስንብት፣ አንድ ሰራተኛ ከደረጃ ተነስቷል። እንዲሁም አንድ ነፃ በድምሩ በ52 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ ቀሪ 54 ሰራተኞችና ኃላፊዎች ጉዳይ በሂደት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

(መልካሙ ከፋለ)

በኲር ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here