ሁለት አህጉራትን ያጋጠመ ምድር ነው፤ በሁለት ውቅያኖሶች መካከልም የቆመ አነስተኛ የምድር አካል:: የመሬት ድልድይም ይሉታል:: ምክንያቱም በተፈጥሮ የተገኘ የሰሜን አሜሪካ እና የደቡብ አሜሪካ አህጉሮችን ያገናኘ መሬት በመሆኑ እና ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ፓስፊክ ውቅያኖስ አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ነው:: ሪፐብሊካ ዲ ፓናማ ወይም ፓናማ ሪፐብሊክ ይባላል:: በሰሜን ከኮሎምቢያ በደቡብ ከኮስታሪካ ጋር ትዋሰናለች:: በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ትልቅ መልከአምድራዊ ጠቀሜታ ያለው አቀማመጥ ያለው ነው:: የፓናማ ሪፐብሊክ ታሪክ፣ እና ማኅበረ ኢኮኖሚው ከአቀማመጡ ጋር የተቆራኘ ነው::
ፓናማ ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካን በሚያገናኘው የመሬት ድልድይ ላይ ትገኛለች፣ ከኮሎምቢያ እና ከኮስታሪካ ጋር ትዋሰናለች፣ እና ሁለቱም የካሪቢያን እና የፓሲፊክ ውቅያኖስ ዳርቻዎች አሏት። አብዛኛው ህዝብ ምስቲዞ የሚባሉት የተወላጅ ጎሳዎች እና የአውሮፓ ዝርያ ድብልቅ ነው። ከአገሪቱ 10 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ዝርያ ነው። ሀገሪቱ ስምንት ዋና ዋና ተወላጅ ቡድኖች አሏት በአንድ ላይ 12 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ያቀፈ ነው፤ እነርሱም ንጋቤ፣ ጉና፣ ኢምበራ፣ ቡግሌ፣ ዉናን፣ ናሶ ቲጅርዲ፣ ብሪብሪ እና ቦኮታ ይባላሉ።
የቅድመ-ኮሎምቢያ ዘመን
የቅድመ ኮሎምቢያ ታሪክን በደንብ ለመገንዘብ በዘመን ከፋፍሎ ማየት ጥሩ ነው:: በመሆኑም ኮሎምቢያውያን ቅኝ ከገዙበት በፊት እና በኋላ ያለውን ዘመን እንመልከት:: ከ2500 እስከ 1700 ዓመተ ዓለም ድረስ ያለውን ጊዜ ቅድመ ኮሎምቢያውን ዘመን ይባላል:: በዚህ ወቅት ብዙ አይነት ክስተቶች ተስተናግደዋል:: የፓርቲያ ቤይ ተወላጅ ማህበረሰቦች በበፓናማ ማእከላዊ ክልል ውስጥ ያለው የቅድመ-ኮሎምቢያ ተወላጆች የፓርታ ቤይ ተወላጅ ማህበረሰቦች በብዙ የባህል ባለሙዎች ዘንድ ከፍ ያለ ደረጃ የተሰጣቸው ማህበረሰቦች ተደርገው ይወሰዳሉ። ከእነዚህ ማህበረሰቦችም ነበር የጎሳ አለቆች ይመረጡ እንደነበር የአርኪዮሎጅ ግኝቶች ያመላክታሉ::
ዛሬ ፓናማ ተብሎ የሚጠራው ክልል ሞናግሪሎ፣ ኩዌቫ፣ ቺብቻን እና ቾኮንን ጨምሮ በበርካታ የሀገሬው ተወላጅ ቡድኖች ሰፈራ ተደርጎበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። እንደሌሎች ጥንታዊ ባህሎች የፓናማ ተወላጆች ትላልቅ ከተሞችን አልገነቡም ፣ ምንም እንኳን በአሜሪካ አህጉር የመጀመሪያዎቹ የሸክላ ሰሪ ህዝቦች መኖሪያ መሆኗ አይታበልም። በሀገሪቱ ማእከላዊ ክልል ውስጥ የሚገኙት የአርኪኦሎጂ ግኝቶች ስለ እነዚህ ቡድኖች አንዳንድ ማህበራዊ አደረጃጀታቸውን የሚናገሩ ቅርሶችን አግኝተዋል:: በቁፋሮ የተገኙ አንዳንድ ምስሎች እና ጌጣጌጦች በኮሎምቢያ ውስጥ ከሚገኙ የብረት-መገልገያዎች ባህሎች መኖራቸውን እና ምናልባትም እስከ ሜክሲኮ ድረስ ያለውን የንግድ ግንኙነት ይጠቁሙ እንደነበር::
የቅኝ ግዛት ዘመን
ከአስራ ስድስተኛው መቶ ዘመን ጀምሮ ስፔናውያን ፓናማ ከተማን ለማቅረብ እና ወርቅና ብር ከከተማው ወደ ካሪቢያን እና በውቅያኖሶች ዳርቻዎች ወዳሉት ግዛቶችዋ ለማጓጓዝ ከአትላንቲክ እስከ ፓስፊክ ውቅያኖስ ያለውን የተፈጥሮ የፓናማ ቦይ ይጠቀሙ ነበር።
በ 1493 ዓ.ም የስፔን ድል አድራጊ የነበረው ሮድሪጎ ዴ ባስቲዳስ በአሜሪካ ምሥራቃዊ የባህር ጠረፍ ላይ ባደረገው ጉዞ በፓናማ መሬት ላይ አረፈ። በሚቀጥለው ዓመት በስፔን ዘውድ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ጣሊያናዊው መርከበኛ ክሪስቶፈር ኮሎምበስ በአራተኛው ጉዞው አካባቢውን እንደቃኘው መረጃዎች ይጠቁማሉ። በ1501 ዓ.ም ስፔናውያን ክልሉን በቅኝ ግዛት ይገዙ ጀመር:: የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፓውያን ሰፈራም በ1502 ተመሠረተ። ይህን ምድር ስፔናውያን በካሪቢያን በኩል ወደ ፓናማ ሲቲ የንግድ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ይጠቀሙበት ነበር።
ኒው ግራናዳ በ1709 ዓ.ም ሲቋቋም የፓናማ ምድርን እንዲሁም የአሁኗ ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር እና ቬንዙዌላን አካትቶ ነበር። የኒው ግራናዳ ዋና ከተማ ሳንታ ፌ ዴ ቦጎታ ነበር። በቦጎታ ርቀት ምክንያት እና በግዛቱ ላይ ጠንካራ ስልጣን ለመያዝ ባለመቻሉ ቅሬታዎች ተነሱ። ቅሬታዎቹም በፔሩ እንደራሴ እንዲሁም በፓናማ በኩል ነበር የተነሳው። በቦጎታ እና በፓናማ መካከል የነበረው ውጥረት ታላቁ ኮሎምቢያ እስከተመሰረተበት እስከ 1811 ዓ.ም ድረስ ቀጠለ። ታላቁ ኮሎምቢያ የአሁኗን ኮሎምቢያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር፣ ሰሜናዊ ፔሩ፣ ምዕራባዊ ጉየና እና ሰሜን ምዕራብ ብራዚልን ያቀፈ ነበር። የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የቬንዙዌላ ወታደራዊ መሪ ሲሞን ቦሊቫር ነበር። ፓናማ በ1813 ዓ.ም ከስፔን ነፃነቷን አገኘች እናም በዚያው ዓመት ወዲያውኑ ወደ ታላቁ ኮሎምቢያ ተቀላቀለች።
ታላቁ ኮሎምቢያ በ1822 ዓ.ም ከአሥር ዓመታት በኋላ ፈረሰች። ይሁን እንጂ ታላቁ ኮሎምቢያ ከወደቀ በኋላም እንኳ ፓናማ የኮሎምቢያ ሀገር አካል ሆና ቆየች፤ በአሥራ ዘጠነኛው መቶ ዘመን አጋማሽ ላይ ኒው ግራናዳ እና ዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያውን ውቅያኖስ አቋርጦ የሚያልፍ የባቡር ሐዲድ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሱ እና “የአሜሪካ ዜጎች እና ጭነት በነፃ እንዲዘዋወሩ መብት” ሰጥተው ነበር። ይህ የባቡር መስመር ለዩናይትድ ስቴትስ ወርቅ ከምእራብ ጠረፍ ወደ ሰሜን ምስራቅ በፍጥነት ማጓጓዝ ያስችላት ነበር። በተለይ በወቅቱ በግዛቷ ካሊፎርኒያ ወርቅ ተገኝቶ ነበር እና እርሱን ለማጓጓዝ አቋራጭ መንገድ ነበር:: እናም ግንባታው በ 1842 ዓ.ም ተጀምሮ በ 1845 ዓ.ም ተጠናቀቀ::
በ1874 ዓ.ም የፈረንሳይ ባለቤትነት ያለው የኒው ፓናማ ካናል ኩባንያ የራሱን ቦይ ለመገንባት ሞክሮ ነበረ:: ነገር ግን የምህንድስና ተግዳሮቶች ከአካባቢው ጂኦግራፊ ሊሻገሩ ባለመቻላቸው፣ እንዲሁም ብዙዎቹ ሠራተኞች በበሽታ ወድቀው በመጨረሻ ሕይወታቸው እያለቀ በመምጣቱ ፕሮጀክቱ በ1881 ዓ.ም ከሽፎ ነበር።
ነፃነት እና የፓናማ ቦይ
ፓናማ ነፃነቷን ከስፔን በ1817 ዓ.ም አገኘች:: ከፓናማ መገንጠል በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ከኮሎምቢያ ጋር የተፈራረመችው የሃይ-ሄራን ስምምነት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በ1893 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሳብ ያቀረበው እና በ1903 የተፈረመ ነው። ይሁን እንጂ የኮሎምቢያ ሴኔት በስምምነቱ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ቋንቋዎች ውድቅ አደረገው፤ ይህም በመጨረሻ አሜሪካ ለፓናማውያን አመጽ እና መገንጠል ድጋፍ አደረገች:: “ኮሎምቢያ የአሜሪካንን ስምምነት ለቦይ ውል ስትናገር ዩናይትድ ስቴትስ በመጀመሪያ የፓናማ የባቡር መንገድን እንዲይዙ የባህር ኃይል ወታደሮችን ላከች እና በመቀጠል የኮሎምቢያ መንግስት የፓናማ መገንጠልን እንዳያቆም ከለከለች።
ፓናማ ነፃነቷን ስታወጅ እና ከደቡብ አሜሪካ በይፋ ተለይታ እስከ 1900 ዓ.ም ድረስ የኮሎምቢያ አካል ሆና ቆይታለች። ይህ መለያየት የተቀሰቀሰው በኮሎምቢያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ባለው ውጥረት ነበር:: ምክንያቱም ዩናይትድ ስቴትስ ለፓናማ ካናል ዞን የክልልነት መብት ጥያቄ በማቅረቧ ኮሎምቢያ ውድቅ ስላደረገችው ነበር። ይህም ዩናይትድ ስቴትስ “የኮሎምቢያን መንግሥት ሥልጣን እንድትገለብጥ አድርጓታል።… ዩናይትድ ስቴትስ በፓናማውያን በ1900 ነፃነታቸውን እንዲያውጁ አበረታታና ደግፋ ነበር:: ይህም በሀገሪቱ በተለይም በካናል ዞን ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ለማድረግ በማሰብ ተነሳስቶ ነበር:: አበቃን::
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሮጀክቱን ለማስጀመር ንብረቶቹን ከወደቀው የፈረንሳይ አዲስ የፓናማ ካናል ኩባንያ ገዛች፤ የካናል ዞን መብቶችንም ከፓናማ መንግስት በ10 ሚሊዮን ዶላር ገዛች:: በግንባታው ሂደት ውስጥ ከሰባ አምስት ሺህ በላይ ሰዎች በካናል ላይ ሠርተዋል። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ከምእራብ ህንዶች የመጡ ሠራተኞች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከአውሮፓ አገሮች በተለይም ከጣሊያን እና ከስፔን የመጡ ናቸው። ከአሥር ዓመታት በላይ ከተገነባ በኋላ፣ በግምት 387 ሚሊዮን ዶላር ወጪ፣ የፓናማ ካናል በነሀሴ 1906 ዓ.ም በይፋ ተከፈተ:: ይህ ቦይ የዘመናችንን የምህንድስና ልህቀት ማሳያ የሆነ ምድራችን የሰው ልጅ ድንቅ ስራ ነው:: የፓናማውያንን እና የዓለምን ታሪክ የቀየረ ነው::
ሳምንቱ በታሪክ
ኢትዮጵያ የቀይ መስቀል
ኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማህበር አባል የሆነችው መስከረም 15 ቀን 1928 ዓም ላይ ነበር፡፡ ይህም የጄኔቫው ስምምነት ከተፈረመ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ እናም ዓለማቀፋዊ እውቅናን አግኝቶ በዓለም 48ኛው ማህበሩን የተቀላቀለች ሀገር አድርጓታል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የቀይ መስቀል ማህበር በመመስረት ረገድ እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ይጠቀሳሉ፡፡ ከአድዋ በኋላ በርካታ የሰብአዊ ተግባራትን በመከወን ማህበሩ በሀገሪቱ ይታወቅ ነበር ፡፡ በዐፄ ምኒልክ ዘመን የመጀመሪያው የቀይ መስቀል አገልግሎት በተለይ ከአድዋ ጦርነት ቆስለው የተመለሱ አርበኞችን የህክምና እርዳታ በመስጠት አገልግሏል፡፡
ኒክሰን እና ኬኔዲ
መስከረም 16 ቀን 1951 ዓ.ም በአሜሪካ የፕሬዝደንትነት ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ ጆን ኤፍ ኬኔዲ እና ሪቻርድ ኒክሰን ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዝን በተላለፋ የምረጡኝ ዘመቻ ክርክር ሲያደርጉ ለእይታ ቀርቧል፡፡ በዚህ ክርክር ኬዲ አሸንፎ የአሜሪካ መሪ ሆኗል፡፡
(መሰረት ቸኮል)
በኲር የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም