1ኛ ዙር ግልጽ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ1ኛ ዙር የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. የጨረታ ቁጥር ደም/ከ/መ/ል/01/17
  2. የጨረታ ዙር 1ኛ
  3. የጨረታ አይነት መደበኛ
  4. የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል ሶስት በአንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘሩት መሠረት ለመኖሪያ፣ ለቅይጥ መኖሪያ ለንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ /ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 24/06/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል በደም/ከተ/መ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 99 በሥራ ሰዓት መግዛት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ነው፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ነው፡፡
  7. ቦታውን መጐብኘት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልጽ መርሃ ግብር መሠረት የምናስጐበኝ ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ በ11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተዉ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  9. በጨረታዉ የውጭ አገር ዜጎች መጫረት አይችሉም፡፡
  10. በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ አሸናፊነቱ ተገልጾ እያለ ቀርቦ ውል ያልፈጸመ በዚህ ጨረታ የማይሳተፍ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ሰላሳ በመቶ እና ከዚያ በላይ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋና ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  13. በጨረታ ለተሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊ ከተረጋገጠበት /ከተገለጸበት ከሚቀጥለዉ ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማንነታቸዉን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 773 00 02 /391 /09 44 12 29 22 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here