በሰሜን ወሎ ዞን የሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት እቃዎች ፣የፅህፈት መሳሪያዎች ፣የደንብ ልብስ ፣ኤሌክትሮኒክስ እና ህትመት ቅፃቅፅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ጥራት ያላቸው እቃዎችን ማቅረብ አለባቸው፤ ያአቀረቡት እቃዎች ጥራት የሌላቸው ከሆኑ የመቀየር ግዴታ አለባቸው፤ የተገዙ እቃዎችን የሚገጣጠሙ ከሆኑ የመገጣጠምና የመገጣጠምን ወጭ በራሳቸው ይሸፍናሉ ፡፡
- የጨረታ ሰነዶች ዋናውን በፖስታ በስም በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- የግዥ መጠኑን ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የባት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸው ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ማስከበሪያ አንድ በመቶ፣ የውለታ ማስከበሪያ 10በመቶ በሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፤ሆስፒታሉ በውስጥ ገቢ ደረሰኝና ሲፒኦ የሰነድ ማስከበሪያ ካላስያዙ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይሆናል ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ሰነዶች መቄት ወረዳ ሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላል ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚገባበት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጥዋቱ ከ2፡30 እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ይሆናል ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡15 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 89 ይከፈታል ፤16ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1 /2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች 20በመቶ የመቀነስ እና የመጨመር መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ለማቅረብ ውል በፍትህ መውሰድ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ መቄት ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ድረስ እቃውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊዎች ያአሸነፉትን እቃ ሆስፒታሉ አይቶ በሎት ወይም ድምር አሸናፊ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 033 211 07 26 ወይም 092 896 03 49 /09 41 82 69 81 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ የሚገባው በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት የሚገኘው ሳጥን ነው፡፡
መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

