የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ሎት 1 የቢቡኝ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የቢሮ ጥገና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ (የሙያ ፈቃድ ወይም ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ለግንባታው የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና ደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ)፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
የጥገና ስራ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጥገና ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከየካቲት 09/2018 እስከ የካቲት 29/2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ22 ኛዉ ቀን የካቲት 30/ 2018 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
ለግንባታ ጨረታው በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም (በ2014 በጀት ዓመት ተሻሽሎ የወጣውን የግንባታ መመሪያ ተግባራዊ ይሆናል)
የቅድሚያ ክፍያ 30 በመቶ አይከፈለውም፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 00 47 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

