ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደ/ወ/ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የጉራንባ ጤና ጣቢያ ተቋርጦ የቆየዉን ግንባታ ለማስቀጠል ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከየካቲት 162018 ዓ/ም ጀምሮ የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የግንባታዉ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከየካቲት 16/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 6/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10. በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት መጋቢት 7/2018 ዓ.ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን መጋቢት 7/2018 ዓ/ም 4፡00  ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟለት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታዉ ማሸነፈቸዉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ከማህንዲሉ ግምት በታች 25 በመቶ ዝቅ አድርጎ ከሞላ የዉል ማስከበሪያ 25 በመቶ ማስያዝ እና ቅድመ ክፍያ የማይከፈለዉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ እንዲሁም ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
  14. በጨረታዉ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here