በአፈ/ከሳሽ ዩሀንስ ገረም እና በአፈ/ተከሳሽ ጌትነት ዳኛው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአገው ግ/ቤት ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በስሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኘው በአቶ ጌትነት ዳኛው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 3,920,286 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር) ስለሚሸጥ በጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያው ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም ወጥቶ እስከ መጋቢት 16/2018 ዓ/ም ለ30 ቀን ቆይቶ ጨረታው መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ 6፡30 የሚካሄድ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታ ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 በሲፒኦ ይዛችሁ እንድቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

