ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ ሎት 1. በቡሬ  ደምበጫና ፍ/ሰላም ከተሞች መጋዝን፣ ቢሮ፣ የጥበቃ ቤት፣ የመጸዳጃ ቤትና የአጥር ግንባታ እና የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ግንባታውን ለማስገንባት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ለማሰራት አስፈላጊውን የሰው ኃይል ህትመቶችን አቅርቦት አሟልተው መወዳደርና መስራት የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ሎት 2. የ2018 ዓ/ም ምርት ዘመን 5,000 ኩ/ል የስንዴ ሰብል ሽያጭ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ  ተወዳዳሪዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ለማማከር አገልግሎት የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለ2018 ዓ/ም የታደሰ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆነ አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (የቲን) የቫት ምዝገባ መለያ ቁጥር (ቫት ሠርተፊኬት)፤ 6 ወራት ያልሞላው የቫት ክሊራንስ የዘመኑን ግብር ስለመገበራቸው የሚያሳይ የግብር ክሊራንስ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት በአካባቢው ተጽዕኖ ግምገማና ተዛማች ሥራ ቢያንስ አንድ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የሚሞሉት የጨረታ ዋጋ ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለባቸው፡፡
  2. በዚህ የመማክር ጨረታ መሳተፍ የሚችሉት አማካሪዎች በዘርፉ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለባቸው እናስታውቃለን፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪጅን መውሰድና ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በሁለት ኮፒ ዋና እና ኦርጅናል አያይዘው በማሽግ ማቅረብና ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. በውክልናው የሚጫረቱ ተጫራቾች ግልጽና የማያሻማ ውክልና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጨረታ ኮሚቴው በውክልናው ላይ ጥርጣሬ ካደረበት ተጨማሪ ማስረጃ ሊጠይቅ ወይም ሊያጣራ ይችላል፡፡
  5. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች ባቀረበው የሥራ ዝርዝር መሰረት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ነው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀኑ በእለቱ በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጓለም፡፡
  8. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለጸላቸው በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የደንብ ዋስትና የተወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ማስከበሪያ ማሰገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረጉ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ለስንዴ ሽያጭ ሎት 2. የማንሻ ቦታ ቡሬ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው መጋዝን ሲሆን የመጫኛና ልዩ ልዩ ወጪዎችን ገዥ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  11. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ነገሮችን ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here