ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ም/ቤት ህንፃ አስ/አጠ/ማዕከል ለመብራት አገልግሎት የሚዉሉ ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቱን የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም፣ አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በጨረታው የተሳተፈ ማንኛውም ድርጅት ዋጋ ካቀረበ በኋላ ዋጋውን መለወጥና ማሻሻል ወይም በጨረታው አልሳተፍም ቢል ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ተመላሽ አይሆንም፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሠከረለት Cash Payment order (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ስራ አፈጻጸም ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፋበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ በሚቀጥለው 10 ተከታታይ ቀን  (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ  ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፡፡ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ በዚሁ እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  10. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  11. በዋጋ መሙያዉ ሥርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ሌሎች በዚህ መመሪያ ያለተገለፁ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 226 21 51 /058 222 14 38 በመደወል ወይም በፖ.ሣ.ቁ 1324 በመላክ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ም/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here