በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በአውሮፓ ዩኒየን የበጀት ድጋፍ ሎት 1. በሹራ ቀበሌ አነስተኛ መስኖ ጠለፋ፣ ሎት 2.በሹራ ቀበሌ 5 በአፀይተራ ቀበሌ 4 በቃላይ ቀበሌ 1 የእጅ ጉድጓድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- በጨረታው ለመወዳደር መስፈርቱንም የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ለመስኖ ጠለፋው ደረጃ 5 እና ከዚያ ሲሆን ለንፁህ ውሃ መጠጥ ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ጨረታ ለመስኖ የፋይናሻልና ቴክኒካል ይጠይቃል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነዱን ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ቀን ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣትና ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጉልህ በተፃፈ አድራሻ ምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ምዕራብ በለሳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ከረዳት ገንዘብ ያዥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ከስነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በተራ ቁጥር 6 ከተገለፀው ተቋም ማስያዝ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊቱ ልዩ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ፖስታው ላይም ሆነ ከጨረታ ሰነዱ ስም ፊርማ፣ ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሙሉ አድራሻውን መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የውሃ ግንባታው የእጅ ዋጋን እና የማቴሪያልን ጨምሮ ሙሉ ግንባታ ነው፡፡
- ይህ ጨረታ በክልሉ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር መመሪያ የሚተዳደር ይሆናል፡፡
- ጨረታው ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

