በደሴ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው አዝዋ ስርት ኃ/የተ/መሰረ/ሸማቾች ህ/ስ/ማህበር 1. በቧንቧ ውሀ ክ/ከተማ ፔፒሲ ፋብሪካ አካባቢ ለሱቅ ለግሮሰሪና ምግብ ቤት እንዲሁም ለመኝታ አገልግሎት የሚውሉ ከ45 በላይ ከፍሎች ያሉት ባለ 5 ወለል ህንፃ እና 2. በመናፈሻ ክ/ከተማ ተርሚናል ኮንዶምንየም ህንፃ ላይ አንድ ክፍል የንግድ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ተጫራቾች ክዚህ በታች የተዘረዘሩ ዋና ዋና ጉዳዮች ሊገነዘብ ይገባል፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 16/2018 ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ሲሆን ጨረታው መጋቢት 4/2018 ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡45 ይከፈታል፡፡
- መግዛት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከየካቲት 16/2018 ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ቤቶቹን ባሉብት ሁኔታ በካል በመገኘት መጎብኝት ይችላሉ፡፡
- መግዛት ስለሚፈልገው አይነት ዝርዝር መረጃ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ስለሚችሉ ሰነዱን ቧነቧ ውሀ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ አካባቢ በሚገኝው የማህብሩ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ለህንፃው ሰነድ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ለኮንደምንየም ቤት ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ቫትን ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዘ አለባችው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ በተለያዩ በሰምና በጥንቃቄ የታሸገ ፖስታ ህንጻው ጋር ለዚሁ ጉዳይ በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ መጋቢት 4/2018 ከረፋዱ 3፡20 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሻትን ጨምሮ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ማስከበሪያ ዋስትና የተቀመጠበት ባንክም ዋስትናውን ማስቀመጡን በደብዳቤ ማረጋግጫ መስጠት ይኖርበታል፡፡ የስም ማዛውሪና ተያያዥ ውጪዎችን ገዥ ይሸፍናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ የተገልፀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኃላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታ የሚያገል ከሆነና በሻጭ ማህበር ውል እንዲፈርም ሲቀርብለት ፈቃደኛ ካልሆነ ያሲያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሽያጭ ማህበር ይውርሳል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ማህብሩ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 14 71 82 91 /09 14 60 47 70 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዝዋ ስርት ኃ/የተ/መሰረ/ሸማቾች ህ/ስ/ማህበር

