ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

በምዕራብ ጎጃም መስተዳደር ዞን በፍ/ሠላም ከተማ አስተዳደር የፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የግዥ /ፋ/ን/አስ/ቡድን ለኮሌጁ ለማሰልጠኛ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎች ሎት 1.  የህንፃ መሳሪያ እቃዎች  ሎት 2. የእንስሳት ህክምና መገልገያ   ዕቃዎች  ሎት 3.  የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች  ሎት4 . የአውቶ ሞቲቭ  እቃዎች   ሎት5.  የጣዉላ ዉጤቶች   በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለዉ እና የግዥዉ መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህብር/ በላይ ከሆነ የቫት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፤
  4. ተጫራቾች ለሞሉት የመወዳደሪያ ጠ/ዋጋ መጠን 1በመቶ- 2በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮሌጁ ስም በገቢ ደረሰኝ ገቢ አድርገዉ የደረሰኙን ኮፒ ከጨረታ ፖስታዉ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉን በጥንቃቄ በፖስታ አሽገዉ ስማቸዉን ፣አድራሻቸዉን፣የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸዉን በእያንዳንዱ ዋጋ መሙያ ገፅ ላይ በማስቀመጥና ኮሌጁ ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ከሎት 1–5 በየሎቱ የማይመለስ 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መግዛት ይችላሉ በተጨማሪም የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች በሌላ ተወዳዳሪ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት አይችልም፡፡
  8. ጫረታዉ የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ  ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊዉ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ብር 10 በመቶ በመክፈል ዉል ይዞ የአሸነፈበትን ዕቃ በታዘዘዉ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ ዕቃዉን የምንረከበዉ ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲሆን ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ የሚያቀርብ ነጋዴ ዕቃዉን የማንቀበል መሆኑን አዉቆ ለሚደርሰዉ ኪሳራ ኮሌጁ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. አሸናፊ የሚለየዉ በየሎቱ በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ሲሆን በሎት የተዘረዘሩት ዕቃዎች በሙሉ ያልሞላ ከጨረታ ዉጭ ይሆናል፡፡
  11. ኮሌጁ ጫረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያዉ ላይ ያልተገለፁ ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያዉ ተገዥ መሆን አለባቸዉ፡፡
  12. ኮሌጁ በግዥ መመሪያዉ መሰረት በእያንዳንዱ ዕቃ ላይ 20በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0920245679 /0920041207 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-በዋጋ መሙያ ሰንጠረጁ ላይ ከተጠቀሰዉ ዝርዝር ስፔስፍኬሽን ዉጭ በመሰረዝና በመደለዝ የራሱን ስፔስፍኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከዉድድር ዉጭ ሆኖ በተጨማሪም ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here