አፈ/ከሣሽ አቶ ያዛቸው ምስክር ያለው እና አፈ/ተከሣሽ አቶ አስፋው አዱኛ ያየህ መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሣሽ ስም በዳግማዊ ምኒሊክ ክ/ከተማ ምድረ ገነት ቀበሌ ተመዝግቦ የሚገኘው በምሥራቅ አደራው ጐሽየ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ጊወን ጀንበሬ እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው G+2 200 ካሬ ሜትር ቤት በመነሻ ዋጋ 13‚203‚052.80 (አስራ ሶስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሶስት ሺህ ሃምሣ ሁለት ብር ከ80/100 ሣንቲም) ሆኖ በጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋውን በመያዝ ከጨረታው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታው ቀንም መጋቢት 19/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች በተገለፀው ቀንና ሰዓት ንብረቱ ከሚገኙበት ቦታ ዶናበር ት/ቤት አካባቢ ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

