ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱት ተበዳሪዎች ያለባቸውን ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት ተቋሙ አነስተኛ የፋይናነስ ስራ አዋጅ ቁጥር 626/2001 እና አዋጅ ቁጥር 97/1990 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ብድሩን በዋስትና ወይም በመያዣነት የተያዘውን የመኖሪያ ቤት በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪው
ስም |
የንብረት አስያዥ ስም | የንብረቱ አይነት | የቤቱ ስፋት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ | ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ |
| ሰርጸ ድንግል ቅርንጫፍ | አቶ ቀለቡ ንግሩ ደሴ አቶ አዲሱ ንግሩ ደሴ
እና አቶ አብርሃም ቻላቸው ከልካይ
|
አቶ ቀለቡ ንግሩ ደሴ | የመኖሪያ ቤት | 150 ካ.ሜ | 2,944,640.86 | ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሰርጸ ድንግል ቅርንጫፍ መጋቢት 23/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 5፡00 |
ማሳሰሰቢያ፡-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል የሐራጁን 5 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ይህን ካላደረገ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ ሳይሆን ውሉ ይቋረጣል፡፡
- ሐራጁ የሚካሄድበት በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፋሲሎ ክፍለ ከተማ 03 ቀበሌ ሰርጸ ድንግል ቅርጫፍ ጽ/ቤት፡፡
- በጨረታው ላይ ተጫራቾችና ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎችቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በመንግስት የሚፈለጉ ግብሮችን ፣ የስም ማዛወሪያዎችን እና ሌሎች ወጭዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-583 209 021 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ

