በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእናርጅና እናውጋ ወረዳ የደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል፡- 1.የጽህፈት መሳሪያ፣ 2.የህንጻ መሳሪያዎች፣ 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 4. የኤሌክትሪክ እቃዎች 5.የግብርና እቃዎች፣ 6. የጋርመንት እቃዎች እንዲሁም 7. የሀውስ ሆልዲንግ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፋሉና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠናቸው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሚሞሉበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ 1 ገቢ አድርገው መሂውን ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ዉስጥ የዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል መፈረም አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ላይ የጨረታው ሳጥን ታሸጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓል ቀን እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የእቃዎችን አጠቃላይ የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን ደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማቅረብ አለበት፡፡
- ኮሌጁ አንደ አስፈላጊነቱ በሎትም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 75 78 75 /09 35 48 41 11 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

