ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

የምዕራብ ጎጃም ዞንና አካባቢው አማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት crisis-affected children are protected from violence, explotation, abuse, neglect, and haremtul practices ከተባለ ግብረ- ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በወንበርማና ሰከላ ወረዳዎች እየሰራን እንገኛለን፡፡ ለዚህ ተግባር ግብዓት አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ፈርኒቸር፣ የመኝታ ቁሳቁስ እና ኮምፒውተር በሎት በመለየት በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ምዕ/ጎጃም ዞን /አካ/ አልማ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መሰረት በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በምዕ/ጎጃም ዞን/አካ/አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ8 ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ለሚሰራው ስራ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ሲፒኦ ካስያዘ በኋላ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎችን ወንበርማና ሰከላ ወረዳዎች ድረስ በመከፋፈል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. የዕቃውን ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ጋር ማግኝት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በሎት በድምር ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  9. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 29 28 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሳቢያ፡- ሰነዱ የሚሸጥበት ቦታ ምዕ/ጎጃም ዞንና አልማ ልማት ጽ/ቤት እና ባ/ዳር አልማ ዋናው መ/ቤት ህንጻ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር 09 ሲሆን ሰነድ የሚመለስበት ቦታ ምዕ/ጎጃም ዞንና አልማ ልማት ጽ/ቤት ነው፡፡

የምዕ/ጎ/ዞንና አካ/አማራ ልማት ማህበር ማ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here