ፀደይ ባንክ (ኢማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ለአቶ ጌትነት መንግስት እና ወ/ሮ ገነት ባይነሰኝ ለሰጣቸው ብድር በዋስትና የያዘውና በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተጠቀሰው መኖሪያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፉት በሕግ ሰውነት ያገኙ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃለጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንክ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከሄዱ በፊት ቤቱን በባንኩ አማካኝነት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ የፀደይ ባንክ አማ እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ከሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግባት መጠየቅ ይችላል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 227 07 08 እና 09 10 30 03 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
| የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጪ ስም | የካርታ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝበት ቦታ | የቦታው ስፋት በካ/ሜ | የንብረቱ አይነትና አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታው ቀንና ሰዓት | ጨረታው የወጣው |
| ጌትነት መንግስት እና ገነት ባይነሰኝ | ጌትነት መንግስት እና ገነት ባይነሰኝ | 1190/13 | አዘና ከተማ 01 ቀበሌ | 500 ካ/ሜ | ድርጅት | 5,688,88.0.73 | 24/07/2018 ዓ.ም ከ4፡00-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
ፀደይ ባንክ (ኢማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ

