ፀደይ ባንክ አ/ማ አዘና ቅርጫፍ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለተበዳሪዎች ይበሉ ሽባባው እና አበባ ወርቅነህ፣ የትዋለ አይኔ እና አዳነች ታምር፣ ይርጋለም ገረም እና ታሪክ እጅጉ እንዲሁም አደራው ወሲሁን ብዙአየሁ ንጉሴ ለሰጠው ብድር በውል ስምምነት መሰረት መክፈል ስላልቻሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የንብረቱ አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርጫፍ | ለጨረታው የቀረበው ንብረት | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የካርታ ቁጥር | የቦታው ስፋት በካ/ሜ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት | ጨረታው የወጣው
|
||
| ቀን | ሰዓት | ቦታ | ||||||||||
| 1 | አደራው ዋሲሁንና ብዙአየሁ ንጉሴ | አደራው ዋሲሁንና ብዙአየሁ ንጉሴ | አዘና ቅርጫፍ | መኖሪያ ቤት | አዘና ከተማ 01 ቀበሌ | 1401/14 | 500 ካ/ሜ | 467,076.62 | 25-07-2018 | 4፡00-6፡00 | እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 2 | ይርጋለም ገረምና ታሪክ እጅጉ | ይርጋለም ገረምና ታሪክ እጅጉ | አዘና ቅርጫፍ | መኖሪያ ቤት | አዘና ከተማ 01 ቀበሌ | ማ/ህ36/2007 | 200 ካ/ሜ | 578,858.08 | 25-07-2018 | 4፡00-6፡00 | እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 3 | የትዋለ አይኔ እና አዳነች ታምር | የትዋለ አይኔ እና አዳነች ታምር | አዘና ቅርጫፍ | መኖሪያ ቤት | አዲስ ቅዳም ከተማ | 676/11 | 233.75 ካ/ሜ | 438,470.76 | 25-07-2018 | 4፡00-6፡00 | እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ | ለመጀመሪያ ጊዜ |
| 4 | ይበሉ ሽባባው እና አበባ ወርቅነህ | ይበሉ ሽባባው እና አበባ ወርቅነህ | አዘና ቅርጫፍ | መኖሪያ ቤት | አዲስ ቅዳም ከተማ | 765/11 | 240 ካ/ሜ | 331,114.65 | 25-07-2018 | 4፡00-6፡00 | እንጅባራ ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ | ለመጀመሪያ ጊዜ |
ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቃላ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሽናፊ አሽናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ የፀደይ ባንክ አማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የስበሳባ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ከሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 እና 09 23 22 28 94 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፀደይ ባንክ አ/ማ እንጅባራ ዲስትሪክት

