የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች ማለትም ሎት 1 የስፖርት እቃዎች እና ሎት 2 የኮንስትራክሽን እቃዎች ከዚህ በታች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የእቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊቱን ከተገለፀ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላዉን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከየካቲት 23/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 08/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 መጋቢት 08/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካክሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር መቀነስ ይችላል እንዲሁም ማንኛውም ተጫራች ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃውን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት ፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

