በምሥራቅ ጎጃም አሥተዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን በወረዳችን ሥር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ከ2018 የመደበኛ በጀት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የጽህፈት መሣሪያ እንዲሁም በወረዳ ስፖርት ምክር ቤት በጀት የስፖርት ትጥቅና የስፖርት ጫማ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይዘጋና በዕለቱ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ የግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለያአንዳንዱ ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) እና ለስፖርት ትጥቅና ለስፖርት ጫማ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ብቻ በመ/ቤታችን መሂ 1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ በመ/ቤቱ መሂ 1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በአድራሻ ለደ/ኤ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በማድረግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የታደሰ ንግድ ፈቃድና ቲን ምዝገባ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማያያዝ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ30 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ የአሸነፈውን እቃ የደ/ኤ/ወ/በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውድድሩ በጥቅል በዋጋ ድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጋችሁ በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

