የጨረታ ቁጥር፡- 005/2018
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ በጀት ለቢሮ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶበዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 87 ዘወትር በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮቀበሌ 07 ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ

