ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

በጎንደር ከተማ አስተዳደር በጤና መምሪያ ሥር የሚገኘው የጎንደር ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ከላይ 1-3 የተዘረዘረውን ፎቶ ኮፒ እና ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የግዥውን መጠን እንደአስፈላጊነቱ 20 በመቶ መጨመርና መቀነስ ይችላል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከየካቲት 23/2018 እስከ መጋቢት 7/2018ዓ.ም ባለው ተከታታይ ቀን ሰነዱ በሚመለከተው ሰው ተሞልቶ ፊርማና ማህተም ተደርጎበት በጎንደር ጤና ጣቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው የሚያበቃው መጋቢት 7/2018 ዓ.ም የሥራ ቀን ሲሆን መጋቢት 08/2018 ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል፡፡
  8. ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ ናሙና ማቅረብ ወይም ማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካልቀረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃውን  ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ውድቅ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ለጽዳት እቃ ብር 18,230.64 (አስራ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር ከ64/100) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ለጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ብር 16,380 (አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ በመክፈል ጎንደር ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  14. በድርጅቱ ውስጥ የሌለ እቃ አለኝ ብሎ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች በዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  16. አድራሻችን በጎንደር ጤና ጣቢያ በተለምዶ ፖሊ ጤና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ
    058 111 06 54 /09 20 34 77 77 በመደውል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ  የቫት ተመዝጋቢ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ በመጨመር ሰነዱ ላይ ይቅረብ፡፡

የጎንደር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here