በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት 1. የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር፣ 2. ዲጅታል ቪዲዮ ካሜራ እንዲሁም 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ 50 በመቶ የሚቆረጥባቸው መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15 ኛዉ ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 14 በ16ኛዉ ቀን በ3፡00 ታሽጐ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 320 58 38 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 71 04 ወይም 058 226 60 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 13 ከእስፖርት ኮሚሽን ጀርባ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

