ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
165

ቁጥር 14/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ሎት 1 የአሚኮ የአጥር ግንባታ ሥራ  ደረጃ 6 እና በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ሎት 2 የደሴ ስቱዲዩ የኢንቴረር ሥራ ደረጃ 6 እና በላይ ሁኖ ደረጃ 8 የህንጻ ማጠናቀቅ ፈቃድ ያላቸዉ ወይም ማቅረብ የሚችሉ፣ ሎት 3 የአዳራሽ ኮርኒስ እና የቴሌቪዥን ህንጻ ዉስጥ የሚገኙ ኮርኒስ ስራ ደረጃ 7 እና በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎችን እንዲሁም ሎት 5 የጽህፈት መሳሪያ ፈቃድ ያለቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለግንባታ ሥራዎች የከተማ ልማት የብቃት ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 1፡ ሎት2 እና ሎት 3 በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ ቀናት) አንዲሁም ሎት 4 እና ሎት 5 በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ  ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106  መግዛት ይችላሉ፡፡ የፋይናንስ ሰነዶችን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በፖስታ  በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን  ሎት 1፣2 እና 3 በ22 ተኛዉ  እና ሎት 4 እና 5  በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው ለሎት 1፣2 እና 3 በ22ኛው ቀን ሎት 4 እና 5 በ16 ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30  ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ሎት 1፣2 እና 3 በ22ኛዉ እና ሎት 4 እና 5 በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉትን የአጥር ግንባታ ስራ፣ የደሴ ኢንቴረር ስራ፣ የአዳራሽ ኮርኒስ ስራ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ዓይነት ብዛትና (ስፔስፊኬሽን) እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here