ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አሚኮ በቁጥር ኮ/አ/ም/ስ/ኤ/299/2018 በቀን 26/05/2018 ዓ.ም በሰጡን ውክልና መሰረት ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ፈርኒቸር እና የፈርኒቸር ዉጤቶች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (La Payer ldentificatin Number) ያላቸዉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት (Value Added Tax certificate) የተመዘገቡ መሆናቸዉን፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታዉ የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ክ/ሂ/ማ/ደ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መወዳደር የማይችሉ መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናዉ አሸናፊዉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እንዲሁም የዉል ማስከበሪያ ዋስትናዉ ዉሉ ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ጸንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናዉን የገቢ ደረሰኝ ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠዉ ዝርዝር መግለጫ ዉጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ ሃያ አንደኛዉ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናዉን በዋግ ኸምራ ብ/አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግን/አስር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በአሰራ ስድስተኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዋኽ ብ/አስ/ር ገ/ኢ/ት መምሪያ ግን አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በአሰራ ስድስኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸዉን ለማሻሻል ወይም ከጨረታዉ ለመዉጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸዉ አምስት ቀን በፊት በጽሁፍ ሊያሳዉቁ ይገባል፡፡
  11. መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ይህም ሲባል ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/ኢ/ት/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 12 30 /02 49 /00 62 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here